Background

የላይ ጋይንት ወረዳ ነባራዊ ሁኔታ

የላይ ጋይንት ወረዳ በአማራ ክልል በደቡብ  ጎንደር ዞን ከሚገኙት ወረዳዎች አንዱ ሲሆን ወረዳውም ከባህር ዳር 175 ኪ/ሜትርና ከደብረ ታቦር 75 ኪ/ሜትር እርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ወረዳው በምስራቅ መቄት (በሰሜን ወሎ ዞን) ፣ በምዕራብ ጉና በጌምድርና እስቴ ወረዳ (በደቡብ ጎንደር ዞን) ፣ በሰሜን እብናት እና ቡግና ወረዳ ፣ በደቡብ ስማዳና ታች ጋይንት ወረዳ ያዋስኑታል፡፡ የወረዳው  ጠቅላላ የቆዳ ስፋት 1511.82 ስኩየር ኪ/ሜትር ሲሆን የመሬት አቀማመጡም 5% ተራራማ 75%  ደልዳላማ እና 20% ወጣ ገባ/ኮረብታማ/ ሲሆን በአገልግሎት አይነት ሲተነተን ለእርሻ ሰብል 28 የሚውል ሲሆን የግጦሽ መሬት 13% ለደን እና ቁጥቋጦ 5% ሌላው ቀሪው 54% ተራራማ እና መንደር የሰፈረበት ነው የአየር ንብረት ሁኔታ ስንመለከት ውርጭ 7.6% ደጋ 45.4% ወይና ደጋ 39.4% ቆላ 7.6% ነው፡፡ የአፈር ሁኔታ ቡናማ አፈር 40% ጥቁር አፈር 8% ግራጫማ አፈር 21% ቀይ ቡናማ አፈር 31%ነው፡፡ ወረዳው በ7 ንዑስ ከተማ እና 31 የገጠር ቀበሌ በድምሩ 38 ቀበሌዎችን በመያዝ የተዋቀረ ነው::

ምንጭ ፡- የላይ ጋይንት ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት የስነ-ህዝብ ጥናትና መረጃ መጽሔት 2017 ዓ.ም ዕትም

የላይ ጋይንት ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት አደረጃጀት

Scroll to Top