Values

የላ/ጋ/ወ/አስ/ጽ/ቤት የሚያቅዳቸውን እቅዶች በተሟላ መልኩ ለመፈጸምና በስራ ላይ ለማዋል የሚከተለውን በስራ መርሆዎችና እሴቶች ይከተላል

  • በወረዳችን በየደረጃው እና በሁሉም ሴክተሮችና የስራ መስኮች ብቃት ያለው አመራር ለመፍጠር ጠንክረን እንሰራለን
  • ህዝባዊ ወገንተኝነታችንን በስራ እናረጋግጣለን፣
  • የወጡ የመንግስት ደንቦች ፣ ህጎች ፣ መመሪያዎች በፍትኃዊነት በአግባቡ በሁሉም መስክ እንዲተገበሩ እንሰራለን፣
  • የህገ የበላይነትን እናከብራለን፣
  • የባለጉዳዮችን ጥያቄ በህጋዊ መንገድ በጥሞናና በትህትና አዳምጠን ፣ ወቅታዊና ተገቢ ምላሽ እንሰጣለን
  • በእኩልነት ላይ የተመሰረተ የስርአተ ፆታ መርህን እንከተላለን
  • የህብረተሰቡንና የመ/ቤቱን ሰራተኞች ዲሞክራሲያዊ ተሳትፎ ያረጋገጠ አስራር እንከተላለን፣
  • የግለሰቦችን ጥረትና ተነሳሽነት እንዲጎለብት ጠክረን እንሰራለን፣
  • ተደጋግፎ የመስራት ባህልና መተማመን በመ/ቤቱ ውስጥ እንዲሰፍን እናደርጋለን፣
  • የግለሰብና የቡድን መብትን እናከብራለን
  • የሴቶችን ፍትሀዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እናረጋግጣለን ፣
  • ስርዓተ-ጾታን ማዕከል ያደረገ  ግንዛቤ እንፈጥራለን

Scroll to Top